አንዳንዶቹ በመርከብ ወደ ባሕር ወረዱ፤ በታላቅም ውሃ ላይ ሥራቸውን አከናወኑ፤
መርከቦች በላይዋ ይመላለሳሉ፤ አንተ የፈጠርኸውም ሌዋታን በውስጧ ይፈነጫል።
የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር፣ አንተ አብረከረክሃቸው።
እናንተ ወደ ባሕር የምትወርዱ፣ በዚያም ያላችሁ ሁሉ፣ ደሴቶችና በዚያ የምትኖሩ በሙሉ፣ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፣ ከምድር ዳርቻም ምስጋናውን ዘምሩ።
ቀዛፊዎችሽ፣ ወደ ጥልቁ ባሕር ይወስዱሻል፤ የምሥራቁ ነፋስ ግን፣ በባሕሩ መካከል ይሰባብርሻል።
ያ ሁሉ ሀብት በአንድ ሰዓት ውስጥ ጠፋ።’ “የመርከብ አዛዦች ሁሉ፣ በመርከብ የሚጓዙ መንገደኞች ሁሉ፣ የመርከብ ሠራተኞችና ኑሯቸውን በባሕር ላይ የመሠረቱ ሁሉ በሩቅ ይቆማሉ።