ደግሞም በመሪባ ውሃ አጠገብ እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ ሙሴም ከእነርሱ የተነሣ ተቸገረ፤
በምድረ በዳ ስንት ጊዜ ዐመፁበት! በበረሓስ ምን ያህል አሳዘኑት!
በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ታደግሁህ፤ በነጐድጓድ መሰወሪያ ውስጥ መለስሁልህ፤ በመሪባ ውሃ ዘንድ ፈተንሁህ። ሴላ
ስፍራውንም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፤ እስራኤላውያን ጠብ ፈጥረው፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው ወይስ አይደለም” በማለት እግዚአብሔርን ተፈታትነዋልና።
በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔር እኔን ተቈጥቶ እንዲህ አለኝ፤ “አንተም ብትሆን አትገባባትም።
እግዚአብሔር ግን በእናንተ ሰበብ ተቈጥቶኝ ነበርና አልሰማኝም፤ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ይበቃል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ስለዚህ ነገር አታንሣብኝ።
በእናንተም ምክንያት እግዚአብሔር እኔን ተቈጣኝ፤ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገርና አምላካችሁ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደ መልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ።