ከባላጋራቸው እጅ አዳናቸው፤ ከጠላትም እጅ ታደጋቸው።
በደረቅ ምድር እንዲሻገሩ ባሕሩን በፊታቸው ከፈልህ፤ ያሳደዷቸውን ግን በኀይለኛ ውሃ ውስጥ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ውስጥ ወረወርሃቸው።
እግዚአብሔር የተቤዣቸው፣ ከጠላት እጅ የታደጋቸው ይህን ይበሉ፤
ከጠላቶቻችን እጅ ያዳነን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
ዘወትር በእግዚአብሔር እንመካለን፤ ስምህንም ለዘላለም እንወድሳለን። ሴላ
በዚያች ዕለት እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብጻውያን እጅ አዳናቸው፤ እስራኤልም የግብጻውያን ሬሳ በባሕሩ ዳርቻ ወድቆ ተመለከቱ።
በማይለወጠው ፍቅርህ፣ የተቤዠሃቸው ሕዝብህን ትመራለህ፤ እነርሱን በብርታትህ፣ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ ትመራቸዋለህ።
ከግብጽ አወጣሁህ፤ ከባርነት ምድርም ተቤዠሁህ፤ እንዲመሩህ ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ።
በግብጻውያን ሰራዊት፣ በፈረሶቻቸውና በሠረገሎቻቸው ላይ፣ እናንተን ባሳደዷችሁ ጊዜ በቀይ ባሕር ውሃ እንዴት እንዳሰጠማቸውና እግዚአብሔር ፈጽሞ እንዴት እንዳጠፋቸው አስታውሱ፤