በለመኑትም ጊዜ፣ ድርጭት አመጣላቸው፤ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው።
ያስተምራቸው ዘንድ ቸር መንፈስህን ሰጠሃቸው፤ መናውን ከአፋቸው አልከለከልህም፤ በተጠሙ ጊዜ ውሃ ሰጠሃቸው።
እጅግ የተመኙትን ምግብ በመጠየቅ፣ እግዚአብሔርን በልባቸው ተፈታተኑት።
ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው በእያንዳንዱ ቃል እንጂ፣ በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ሊያስተምርህ አስራበህ፤ አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቁትን መና መገበህ፤
የምድሪቱን ፍሬ በበሉበት ቀን መናው መውረዱ ቀረ፤ ከዚያ በኋላ ለእስራኤላውያን መና አልወረደላቸውም፤ ነገር ግን በዚያ ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።