እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና፤ ትቢያ መሆናችንንም ያስባል።
እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ።
ከምድር ስለ ተገኘህ፣ ወደ መጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ እንጀራህን በፊትህ ላብ ትበላለህ፤ ዐፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ።”
እንደ ሸክላ እንዳበጀኸኝ ዐስብ፤ አሁን ደግሞ ወደ ትቢያ ትመልሰኛለህን?
ነፋስ ያረገፈውን ቅጠል ታስጨንቃለህን? የደረቀውንስ እብቅ ታሳድዳለህን?
መተላለፌን ለምን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ለምን አታስወግድልኝም? ትቢያ ውስጥ የምጋደምበት ጊዜ ደርሷል፤ ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን የለሁም።”
ዘመኔ ምን ያህል ዐጭር እንደ ሆነች ዐስብ፤ የሰውን ልጆች እንዲያው ለከንቱ ፈጠርሃቸው!
ዐፈር ወደ መጣበት መሬት ሳይመለስ፣ መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ አምላክ ሳይመለስ፣ ፈጣሪህን ዐስብ።
እናንተ ነገሮችን ትገለብጣላችሁ ሸክላ ሠሪውን እንደ ሸክላ ትመለከታላችሁ! ለመሆኑ፣ ተሠሪ ሠሪውን፣ “እርሱ አልሠራኝም” ይለዋልን? ሸክላ የሠራውን፣ “እርሱ ምንም አያውቅም” ይለዋልን?