ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤
አምላኬና ንጉሤ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህን ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ።
ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ ቅን ልብ ያላችሁም ሁሉ እልል በሉ።
ሕዝቦች ሁላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር እልል በሉ።
አምላክ በእልልታ፣ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።
ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል ይበል!
ምድር ሁሉ ይሰግድልሃል፤ በዝማሬ ያመሰግኑሃል፤ ለስምህም ይዘምራሉ።” ሴላ
ለሕዝቦች በቅን ስለምትፈርድላቸው፣ ሰዎችንም በምድር ላይ ስለምትመራ፣ ሕዝቦች ደስ ይበላቸው፤ በእልልታም ይዘምሩ። ሴላ
የምድር መንግሥታት ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለጌታ ተቀኙ። ሴላ
ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤
የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፤ እልል በዪ፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ በፍጹም ልብሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ።
እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፣ ስሙም አንድ ብቻ ይሆናል።
በደብረ ዘይት ተራራ ቍልቍል ወደሚወስደው መንገድ በተቃረቡ ጊዜ፣ ቍጥራቸው እጅግ ብዙ የሆነ ደቀ መዛሙርት ስላዩት ታምራት ሁሉ ደስ እያላቸው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እንዲህ እያሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ጀመር፤
ደግሞም፣ “አሕዛብ ሆይ፤ ከሕዝቡ ጋራ ደስ ይበላችሁ” ይላል።
አሕዛብ ሆይ፤ ከሕዝቡ ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳል፤ ጠላቶቹንም ይበቀላል። ምድሪቱንና ሕዝቡን ያነጻልና።