ፌዘኛን የሚገሥጽ ሁሉ ስድብን በራሱ ላይ ያመጣል፤ ክፉውን ሰው የሚዘልፍ ሁሉ ውርደት ያገኘዋል።
አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ፤ “እስራኤልን የምታውክ አንተ ነህን?” አለው።
አክዓብም ኤልያስን፣ “ጠላቴ ሆይ አገኘኸኝን?” አለው። ኤልያስም መልሶ እንዲህ አለው፤ “በእግዚአብሔር ፊት የተጠላውን ነገር ለማድረግ ራስህን ሸጠሃልና አዎን አግኝቼሃለሁ።
ከዚያም የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስ ወጥቶ ሚክያስን በጥፊ መታውና፣ “ለመሆኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በየት በኩል ዐልፎኝ ነው አንተን ያናገረህ?” አለው።
ከዚያም፣ ‘ንጉሡ፣ ይህን ሰው እስር ቤት አስገቡት፤ በደኅና እስክመለስም ድረስ፣ ከደረቅ እንጀራና ከውሃ በቀር ሌላ እንዳትሰጡት’ ብሏል በሏቸው” አለ።
እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነሣሣና ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሣለቁ፤ ቃሉን ናቁ፤ ነቢያቱንም አቃለሉ።
“እነሆ፤ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ ነው፤ ስለዚህ ሁሉን ቻይ አምላክ ተግሣጽ አትናቅ።
ጠቢብ ልጅ የአባቱን ምክር በማስተዋል ይሰማል፤ ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አያዳምጥም።
ፌዘኛ መታረምን አይወድድም፤ ጠቢባንንም አያማክርም።
ከሞኝ ጋራ አትነጋገር፤ የቃልህን ጥበብ ያንኳስሳልና።
ነገር ግን ሕዝቡ ዝም አለ፤ ምንም መልስ አልሰጠም፤ ንጉሡ፣ “መልስ እንዳትሰጡ” ሲል አዝዞ ነበርና።