“የስርቆት ውሃ ይጣፍጣል፤ ተሸሽገው የበሉት ምግብ ይጥማል።”
ሴቲቱ የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዐይን የሚያስደስትና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ፣ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከርሷም ጋራ ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።
ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ይጣፍጠዋል፤ በመጨረሻ ግን አፉን ኰረት ሞልቶት ያገኘዋል።
“የአመንዝራዪቱ መንገድ ይህ ነው፤ በልታ አፏን በማበስ፣ ‘ምንም የሠራሁት ጥፋት የለም’ ትላለች።
ምንጮችህ ተርፈው ወደ ሜዳ፣ ወንዞችህስ ወደ አደባባይ ሊፈስሱ ይገባልን?
ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፤ በልጅነት ሚስትህም ደስ ይበልህ።
ኀጢአት ግን ትእዛዙ ባስገኘው ዕድል ተጠቅሞ በእኔ ውስጥ ማንኛውንም ዐይነት ዐጕል ምኞት አስነሣ፤ ኀጢአት ያለ ሕግ ምዉት ነውና።
በድብቅ የሚሠሩትን ነገር መናገር ራሱ አሳፋሪ ነውና።