ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ናት፤ እግሮቿ ዐርፈው ቤት አይቀመጡም፤
እነርሱም አብርሃምን፣ “ሚስትህ ሣራ የት አለች?” ብለው ጠየቁት። እርሱም፣ “ድንኳን ውስጥ ናት” አላቸው።
ከጨቅጫቃ ሚስት ጋራ በአንድ ቤት ከመኖር፣ በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።
ጥበብ የለሽ ሴት ለፍላፊ ናት፤ እርሷም ስድና ዕውቀት የለሽ ናት።
የእግዚአብሔር ቃል በማንም ዘንድ እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚገዙና ንጹሓን፣ በቤት ውስጥ በሥራ የተጠመዱ፣ ቸሮች፣ ለባሎቻቸው የሚገዙ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው።