ቅናት የባልን ቍጣ ይቀሰቅሳልና፤ በሚበቀልበትም ጊዜ ምሕረት አያደርግም።
ጌታውም፣ “ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ ሚስቱ የነገረችውን ታሪክ ሲሰማ ተቈጣ።
ሴቲቱ ፀነሰች፤ ለዳዊትም፣ “አርግዣለሁ” ብላ ላከችበት።
በቍጣ ቀን ሀብት ፋይዳ የለውም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ትታደጋለች።
ንዴት ጨካኝ፣ ቍጣም ጐርፍ ነው፤ በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?
መደብደብና ውርደት ዕጣው ነው፤ ኀፍረቱም ከቶ አይወገድም።
ምንም ዐይነት ካሳ አይቀበልም፤ የቱንም ያህል ብዙ ቢሆን መማለጃን ዕሺ አይልም።
በልብህ እንዳለ፣ በክንድህም እንደምትይዘው ማኅተም አስቀምጠኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች፣ ቅናቷም እንደ መቃብር ጨካኝ ናትና፤ እንደሚንቦገቦግ እሳት፣ እንደ ኀይለኛም ነበልባል ትነድዳለች።
እነሆ፤ ለብር ደንታ የሌላቸውን፣ በወርቅም ደስ የማይሰኙትን፣ ሜዶናውያንን አስነሣባቸዋለሁ።
“የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ እኔ ለክብሬ በመካከላቸው እንደምቀና ስለ ቀና ቍጣዬን ከእስራኤላውያን መልሶታል፤ ስለዚህ እኔም በቅናቴ ጨርሶ አላጠፋኋቸውም፤
ባሏ የቅናት መንፈስ ዐድሮበት ቢጠረጥርና በርግጥም ጐድፋ ብትገኝ ወይም ባሏ የቅናት መንፈስ ዐድሮበት ቢጠረጥርና እርሷ ግን ጐድፋ ባትገኝ፣
ጌታን እናስቀናውን? በብርታትስ ከርሱ እንበልጣለንን?