በምትሄድበት ሁሉ ይመሩሃል፤ በምትተኛበት ጊዜ ይጠብቁሃል፤ በምትነቃበት ጊዜም ያነጋግሩሃል።
አንተን እንዳልበድል፣ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
ቃልህን አሰላስል ዘንድ፣ ዐይኔ ሌሊቱን ሙሉ ሳይከደን ያድራል።
ምስክርነትህ ለእኔ ደስታዬ ነው፤ መካሪዬም ነው።
በእንግድነቴ አገር፣ ሥርዐትህ መዝሙሬ ናት።
ጕልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል? በቃልህ መሠረት በመኖር ነው።
አቤቱ፤ ሕግህን ምንኛ ወደድሁ! ቀኑን ሙሉ አሰላስለዋለሁ።
ከሰዎች ተግባር፣ በከንፈርህ ቃል፣ ከዐመፀኞች መንገድ፣ ራሴን ጠብቄአለሁ።
በየአቅጣጫው የከበበኝን፣ አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፤ ወደ ተቀደሰው ተራራህ፣ ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ።
የመለየት ችሎታ ይጋርድሃል፤ ማስተዋልም ይጠብቅሃል።