ከተግሣጽ ጕድለት የተነሣ ይሞታል፤ ከቂልነቱ ብዛት መንገድ ይስታል።
ባይሰሙ ግን፣ በሰይፍ ይጠፋሉ፤ ያለ ዕውቀትም ይሞታሉ።
ያለ ጥበብ ይሞቱ ዘንድ፣ የድንኳናቸው ገመድ አልተነቀለምን?’
ስለዚህ በገዛ ዕቅዳቸው እንዲሄዱ፣ አሳልፌ ለደንዳናው ልባቸው ሰጠኋቸው።
በደላቸውን ወደ ራሳቸው ይመልሳል፤ በክፋታቸውም ያጠፋቸዋል፤ እግዚአብሔር አምላካችን ይደመስሳቸዋል።
የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፤ የዕቅዳቸውንም ውጤት ይጠግባሉ።
የጻድቃን ከንፈሮች ብዙዎችን ያንጻሉ፤ ቂሎች ግን በልበ ቢስነት ይሞታሉ።
ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፤ ጠማማ ልብ ያላቸው ግን የተናቁ ናቸው።
ልባቸውን ከጽድቅ የሚመልሱ የእጃቸውን ሙሉ ዋጋ ይቀበላሉ፤ ደግ ሰውም ወሮታውን ያገኛል።
ክፉዎች በክፋታቸው ይወድቃሉ፤ ጻድቃን ግን በሞት ጊዜ እንኳ መጠጊያ አላቸው።
የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣ በሙታን ጉባኤ ያርፋል።