ልጄ ሆይ፤ የምነግርህን አስተውል፤ ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ።
ሕይወትን የሚወድድ፣ በጎውንም ያይ ዘንድ ዕድሜን የሚመኝ ማን ነው?
ሕዝቤ ሆይ፤ ትምህርቴን ስማ፤ ጆሮህንም ወደ አንደበቴ ቃል አዘንብል።
ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን።
ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣ ልብህንም ወደ ማስተዋል ብትመልስ፣
በልብህ ስትጠብቃቸው፣ ሁሉም በከንፈሮችህ ላይ የተዘጋጁ ሲሆኑ ደስ ይላልና።
ልጄ ሆይ፤ ጥበቤን ልብ በል፤ የማስተዋል ቃሌንም በጥሞና አድምጥ፤
ልጄ ሆይ፤ ቃሌን ጠብቅ፤ ትእዛዜንም በውስጥህ አኑር።
ጆሯችሁን ከፍታችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ ነፍሳችሁም እንድትኖር አድምጡኝ። ለዳዊት በገባሁት በጽኑ ፍቅሬ፣ ከእናንተም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።
እርሱ እየተናገረ ሳለ፣ ብሩህ ደመና ሸፈናቸው፤ ከደመናውም ውስጥ፣ “በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ ተሰማ።