አንበጦች ንጉሥ የላቸውም፤ ሆኖም ቅደም ተከተል ይዘው ይጓዛሉ፤
እርሱ በተናገረ ጊዜ አንበጣ መጣ፤ ስፍር ቍጥር የሌለውም ኵብኵባ ከተፍ አለ፤
እንሽላሊት በእጅ ትያዛለች፤ ሆኖም በቤተ መንግሥት ትገኛለች።
አዛዥ የለውም፤ አለቃም ሆነ ገዥ የለውም፤
ከአንበጣ መንጋ የተረፈውን፣ ትልልቁ አንበጣ በላው፤ ከትልልቁ አንበጣ የተረፈውን፣ ኵብኵባ በላው፤ ከኵብኵባ የተረፈውን፣ ሌሎች አንበጦች በሉት።
“በመካከላችሁ የሰደድሁት ታላቁ ሰራዊት፣ ትልልቁ አንበጣና ትንንሹ አንበጣ፣ ሌሎች አንበጦችና የአንበጣው መንጋ የበላውን፣ እነዚህ ሁሉ የበሏቸውን ዓመታት ዋጋ እመልስላችኋለሁ።