የተጠላች ሴት ባል ስታገባ፣ ሴት ባሪያ በእመቤቷ እግር ስትተካ።
መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት፤ አሳፋሪ ሚስት ግን ዐጥንቱ ውስጥ እንዳለ ንቅዘት ናት።
ሞኝ ልጅ ለአባቱ መጥፊያ ነው፤ ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ ጠፈጠፍ ናት።
ከጨቅጫቃና ከቍጡ ሚስት ጋራ ከመኖር፣ በምድረ በዳ መኖር ይሻላል።
ከጨቅጫቃ ሚስት ጋራ በአንድ ቤት ከመኖር፣ በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።
ጨቅጫቃ ሚስት፣ በዝናብ ቀን እንደሚወርድ የማያቋርጥ ጠፈጠፍ ናት፤
ሰው አገልጋዩን ከልጅነቱ ጀምሮ ቢያቀማጥል፣ የኋላ ኋላ ሐዘን ያገኘዋል።
ባሪያ ሲነግሥ፣ ሰነፍ እንጀራ ሲጠግብ፣
“በምድር ላይ አራት ነገሮች ትንንሽ ናቸው፤ ሆኖም እጅግ ጠቢባን ናቸው፤