“የአመንዝራዪቱ መንገድ ይህ ነው፤ በልታ አፏን በማበስ፣ ‘ምንም የሠራሁት ጥፋት የለም’ ትላለች።
ከዚያም ዳዊት መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፤ እርሱ ወዳለበት ገባች፤ ዐብሯትም ተኛ። በዚህም ጊዜ ወርኃዊ የመንጻት ጊዜዋን ፈጽማ ነበር። ከዚያም ተመልሳ ወደ ቤቷ ሄደች።
“ምድር በሦስት ነገር ትናወጣለች፤ እንዲያውም መሸከም የማትችላቸው አራት ነገሮች ናቸው፤
ስለ ሕይወት መንገድ ደንታ የላትም፤ መንገዶቿ ዘወርዋራ ናቸው፤ ለርሷ ግን አይታወቃትም።
“ ‘አልረከስሁም፣ በኣሊምን አልተከተልሁም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ውስጥ ምን እንዳደረግሽ እስኪ አስቢ፣ ምንስ እንደ ፈጸምሽ ተገንዘቢ፤ እንደምትፋንን ፈጣን ግመል ሆነሻል፤