ከዚያም መንገድህን ያለ ሥጋት ትሄዳለህ፤ እግርህም አይሰናከልም፤
ሕግህን የሚወድዱ ብዙ ሰላም አላቸው፤ ዕንቅፋትም የለባቸውም።
እግርህ እንዲሸራተት አይፈቅድም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም።
እግዚአብሔር ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።
የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤ አካሄዱም አይወላገድም።
ሐቀኛ ሰው ያለ ሥጋት ይራመዳል፤ በጠማማ ጐዳና የሚሄድ ግን ይጋለጣል።
የፍትሕን መንገድ ይጠብቃል፤ የታማኞቹንም አካሄድ ያጸናል።
ስትሄድ ርምጃህ አይሰናከልም፤ ስትሮጥም አትደናቀፍም።
በምትሄድበት ሁሉ ይመሩሃል፤ በምትተኛበት ጊዜ ይጠብቁሃል፤ በምትነቃበት ጊዜም ያነጋግሩሃል።
በመካከላቸው ደካማና ስንኩል አይገኝም፤ የሚያንቀላፋና የሚተኛ አይኖርም፤ የወገባቸው መቀነት አይላላም፤ የጫማቸውም ማሰሪያ አይበጠስም።
ፈረስ በምድረ በዳ እንደሚያልፍ ሁሉ፣ እነርሱንም በጥልቁ ውስጥ አሳልፎ መራቸው፤ ስለዚህም አልተሰናከሉም፤
በእግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ፤ በስሙም ይመላለሳሉ” ይላል እግዚአብሔር።