በዕውቀቱ ቀላያት ተከፈሉ፤ ደመናትም ጠልን አንጠበጠቡ።
ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ ደረቁ ምድር ይገለጥ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ።
እግዚአብሔር የሰማይን ጠል፣ የምድርንም በረከት፣ የተትረፈረፈ እህልና የወይን ጠጅ ይስጥህ።
ኖኅ በተወለደ በስድስት መቶኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ቀን፣ በዚያ ቀን የታላቁ ጥልቅ ምንጮች በሙሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤
ከውቅያኖሶች በፊት፣ የውሃ ምንጮች ከመፍለቃቸው በፊት ተወለድሁ፤
ከአሕዛብ ከንቱ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለን? ሰማያትስ በራሳቸው ማካፋት ይችላሉን? አይ! አይችሉም፣ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ነህ፣ ስለዚህም ተስፋችን በአንተ ላይ ነው።
የጽዮን ሰዎች ሆይ፤ ደስ ይበላችሁ፤ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ሐሤት አድርጉ፤ የበልግን ዝናብ፣ በጽድቅ ሰጥቷችኋልና፤ እንደ ቀድሞውም፣ የበልግንና የጸደይን ዝናብ በብዛት ልኮላችኋል።
ስለዚህ እስራኤል ብቻውን ያለ ሥጋት ይኖራል፤ የሰማያት ጠል በሚወርድበት፣ እህልና የወይን ጠጅ ባለበት ምድር፣ የያዕቆብን ምንጭ የሚነካው የለም።