ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናት፤ አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም።
ዛጐልና አልማዝ ከቍጥር አይገቡም፤ የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍም ይበልጣል።
ምሕረትህ ከሕይወት ይበልጣልና፤ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
ወርቁም አለ፤ ቀዩም ዕንቍ ተትረፍርፏል፤ ዕውቀት የሚናገሩ ከንፈሮች ግን ብርቅ ጌጦች ናቸው።
ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል? ከቀይ ዕንቍ እጅግ ትበልጣለች።
ከብር ይልቅ ምክሬን፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ፤
ጥበብ ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናትና፤ ከምትመኙት ነገር ሁሉ አንዳች የሚስተካከላት የለም።
ጥበብ እንደ ርስት መልካም ነገር ነው፤ ጠቃሚነቱም ፀሓይን ለሚያዩ ሰዎች ነው።
የአሁኑ ዘመን ሥቃያችን ወደ ፊት ሊገለጥ ካለው፣ ለእኛ ከተጠበቀልን ክብር ጋራ ሲነጻጸር ምንም እንዳይደለ እቈጥራለሁ።