ገዥ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣ ሹማምቱ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።
ጌታውም፣ “ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ ሚስቱ የነገረችውን ታሪክ ሲሰማ ተቈጣ።
እርሱም ወጣቶቹ በሰጡት ምክር መሠረት፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደባችሁ፤ እኔ ደግሞ የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፣ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው።
ሕዝቡ ግን አልሰሙም፤ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ፊት ካጠፋቸው አሕዛብ የባሰ ክፉ ድርጊት እንዲፈጽሙ ምናሴ አሳታቸው።
ንጉሥ ለፍርድ ዙፋኑ ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ ክፉውን ሁሉ በዐይኖቹ አበጥሮ ይለያል።
የሰሜን ነፋስ ዝናብ እንደሚያመጣ ሁሉ፣ ሐሜተኛ ምላስም ቍጡ ፊት ታስከትላለች።
ነገር ግን እርሱም ሆነ መኳንንቱ የምድሪቱም ሕዝብ በነቢዩ በኤርምያስ አማካይነት የተነገረውን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።
ከዚያም ሳኦል ባለሟሎቹን፣ “ለዳዊት፣ ‘እነሆ፤ ንጉሡ በአንተ ደስ ብሎታል፤ ባለሟሎቹም ሁሉ ይወድዱሃል፤ ስለዚህ ዐማቹ ሁንለት’ ብላችሁ በምስጢር ንገሩት” ብሎ አዘዛቸው።