ልጄ ሆይ፤ ጠቢብ ሁን፤ ልቤን ደስ አሠኘው፤ ለሚንቁኝ ሁሉ መልስ መስጠት እችል ዘንድ።
በቃልህ ታምኛለሁና፣ ለሚሰድቡኝ መልስ እሰጣለሁ።
ስለዚህ እናንተ ነገሥታት ልብ በሉ፤ እናንተ የምድር ገዦችም፣ ተጠንቀቁ።
የሰሎሞን ምሳሌዎች፤ ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል።
ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ሰው ግን እናቱን ይንቃል።
በማስተዋል መልስ ከሚሰጡ ከሰባት ሰዎች ይልቅ፣ ሰነፍ ራሱን ጠቢብ አድርጎ ይቈጥራል።
አስተዋይ ክፉን አይቶ ራሱን ይሸሽጋል፤ አላዋቂዎች ግን በዚያው ይቀጥላሉ፤ ይቀጡበታልም።
ጥበብን የሚወድድ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፤ የአመንዝራዎች ወዳጅ ግን ሀብቱን ያባክናል።
ወንድሜ ሆይ፤ የቅዱሳንን ልብ ስላሳረፍህ ከፍቅርህ ታላቅ ደስታና መጽናናት አግኝቻለሁ።
ከልጆችሽ አንዳንዶቹ ከአብ በተሰጠን ትእዛዝ መሠረት በእውነት ጸንተው እየኖሩ በማግኘቴ እጅግ ደስ ብሎኛል።