በሞኞች አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣ በሰካራም እጅ እንዳለ እሾኽ ነው።
አንተም፣ “መቱኝ፤ አልተጐዳሁም፤ ደበደቡኝ፤ አልተሰማኝም፤ ታዲያ፣ ሌላ መጠጥ እንዳገኝ፣ መቼ ነው የምነቃው?” ትላለህ።
ሞኝን ወይም የትኛውንም ዐላፊ አግዳሚ የሚቀጥር፣ ፍላጻውን በነሲብ እየወረወረ ወገኖቹን እንደሚያቈስል ቀስተኛ ነው።
ለሞኝ ክብር መስጠት፣ በወንጭፍ ላይ ድንጋይ እንደ ማሰር ነው።