በትልቅ ሰው ፊት ከሚያዋርድህ፣ ራሱ፣ “ወደዚህ ከፍ በል” ቢልህ ይሻላልና። በዐይንህ ያየኸውን ሁሉ፣
በተዋረደ መንፈስ ከተጨቈኑት ጋራ መሆን፣ ከትዕቢተኞች ጋራ ብዝበዛን ከመካፈል ይሻላል።
በንጉሥ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤ በታላላቆች መካከል መገኘትም አይመርህ፤
“እላችኋለሁ፤ ከፈሪሳዊው ይልቅ ይህኛው በእግዚአብሔር ዘንድ ጻድቅ ተብሎ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላልና፤ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ግን ከፍ ይላል።”
ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”
ከዚህ በኋላ እነሆ፤ በሰማይ የተከፈተ በር አየሁ፤ ቀደም ሲል እንደ መለከት ሲናገረኝ የሰማሁት ድምፅ፣ “ወደዚህ ና፤ ከዚህም በኋላ ሊሆን የሚገባውን ነገር አሳይሃለሁ” አለኝ።