ማር ስታገኝ በልክ ብላ፤ ከበዛ ያስመልስሃል።
የበላሃት ትንሿ እንኳ ታስመልስሃለች፤ የምስጋና ቃልህንም ከንቱ ታደርጋለህ።
ወደ ባልንጀራህ ቤት እግር አታብዛ፤ ታሰለቸውና ይጠላሃል።
ከመጠን በላይ ማር መብላት ጥሩ አይደለም፤ የራስንም ክብር መሻት አያስከብርም።
እጅግ ጻድቅ፣ እጅግም ጠቢብ አትሁን፤ ራስህን ለምን ታጠፋለህ?
ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ሲችል ቅቤና ማር ይበላል።
ከሚሰጡትም የተትረፈረፈ ወተት ቅቤ ይበላል፤ በምድሪቱም የቀሩ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላሉ።
“እንግዲህ በገደብ የለሽ ሕይወት፣ በመጠጥ ብዛትና ስለ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝልና ያ ቀን እንደ ወጥመድ ድንገት እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤
በመንፈስ ተሞሉ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ ይህ ብክነት ነውና።