አለዚያ ይህን የሚሰማ ያሳፍርሃል፤ አንዴ የጠፋውን ስምህንም ፈጽሞ መመለስ አትችልም።
የምፈራውን መዋረድ ከእኔ አርቅ፤ ደንብህ መልካም ነውና።
ባግባቡ የተነገረ ቃል፣ በብር መደብ ላይ እንደ ተቀረጸ የወርቅ እንኮይ ነው።
ስለ ራስህ ጕዳይ ከባልንጀራህ ጋራ በምትከራከርበት ጊዜ፣ የሌላውን ሰው ምስጢር አታውጣ፤
መልካም ስም ከመልካም ሽቱ ይበልጣል፤ ከልደትም ቀን የሞት ቀን ይሻላል።