ክፋት የሚያውጠነጥን፣ “ተንኰለኛ” ይባላል።
ንጉሡም መልሶ ሳሚን እንዲህ አለው፤ “በአባቴ በዳዊት ላይ ያደረግህበትን ክፉ ነገር ሁሉ ልብህ ያውቀዋል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ክፉ ሥራህ ብድሩን ይከፍልሃል።
ክፋት ቢያስቡብህ፣ ተንኰል ቢወጥኑብህም አይሳካላቸውም፤
ክፉ ነገር የሚያቅዱ ከትክክለኛው መንገድ ይወጡ የለምን? በጎ ነገር የሚያቅዱ ግን ፍቅርንና ታማኝነትን ያተርፋሉ።
ልባቸው ዐመፅን ያውጠነጥናልና፤ ከንፈራቸውም ሸፍጥ ያወራል።
የተላላ ዕቅድ ኀጢአት ነው፤ ሰዎችም ቂልነትን ይጸየፋሉ።
በልቡ ተንኰል ክፋትን የሚያውጠነጥን፣ ምን ጊዜም ጠብ ይጭራል።
ክፋትን የሚያውጠነጥን ልብ፣ ወደ ክፋት የሚቻኰሉ እግሮች፣
የጋጠወጥ ዘዴ ክፉ ነው፤ የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆን፣ ድኻን በሐሰት ለማጥፋት፣ ክፋት ያውጠነጥናል።
ነነዌ ሆይ፤ በእግዚአብሔር ላይ የሚያሤር፣ ምናምንቴ ክፉ መካሪ፣ ከአንቺ ዘንድ ወጥቷል።
ስም አጥፊዎች፣ አምላክን የሚጠሉ፣ ተሳዳቢዎች፣ ትዕቢተኞችና ትምክሕተኞች ናቸው፤ ክፋትን የሚሠሩበትን መንገድ ያውጠነጥናሉ፤ ለወላጆቻቸው አይታዘዙም።