በባልንጀራህ ላይ ያለ ምክንያት አትመስክር፤ በከንፈርህም አትሸንግል።
እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ነቀፋ የሌለበት፣ ቅን፣ እግዚአብሔርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ሰው የለም፤ ያለ ምክንያት እንዳጠፋው ብትወተውተኝም፣ ይኸው ፍጹምነቱን እንደ ጠበቀ ነው” አለው።
ጨካኝ ምስክሮች ተነሡ፤ ስለማላውቀውም ነገር ጠየቁኝ።
ያለ ምክንያት ወጥመዳቸውን በስውር አስቀምጠውብኛልና፤ ያለ ምክንያት ለነፍሴ ጕድጓድ ቈፍረውላታል።
ኀያል ሆይ፤ በክፋት ለምን ትኵራራለህ? አንተ በእግዚአብሔር ዐይን የተናቅህ፣ እንዴትስ ዘወትር ትታበያለህ?
በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
“የሐሰት ወሬ አትንዛ፤ ተንኰል ያለበትን ምስክርነት በመስጠት ክፉውን ሰው አታግዝ።
ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይዘከዝካል።
ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ ውሸት የሚነዛም ሳይቀጣ አይቀርም።
ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ ውሸት የሚነዛም ይጠፋል።
ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤ እውነቱን የሚናገር ግን ጸንቶ ይኖራል።
በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሰክር፣ እንደ ቈመጥ፣ እንደ ሰይፍና እንደ ተሳለ ፍላጻ ነው።
“ቀልዴን እኮ ነው” እያለ ባልንጀራውን የሚያታልል ሰውም እንደዚሁ ነው።
“ ‘አትስረቁ። “ ‘አትዋሹ። “ ‘ከእናንተ አንዱ ሌላውን አያታልል።
“ማንኛውም ሰው በዐደራ የተሰጠውን ወይም በመያዣነት የተቀበለውን በማጕደልና ባልንጀራውን በማጭበርበር ባይታመን፣ እግዚአብሔርንም ቢበድል ወይም ባልንጀራውን ቢቀማው ወይም ቢያታልለው፣
ወይም የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም ቢል ወይም በሐሰት ቢምል ወይም ሰዎች የሚያደርጉትን እንዲህ ያለውን ማንኛውንም ኀጢአት ቢሠራ፣
ጲላጦስም፣ “ለምን? ምን ክፉ ነገር አድርጓል?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱ ግን አብዝተው እየጮኹ፣ “ይሰቀል!” አሉ።
ይህም፣ ‘ያለ ምክንያት ጠሉኝ’ ተብሎ በሕጋቸው የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው።
ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋራ እውነትን ተነጋገሩ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ብልቶች ነንና።
አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋራ አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁ እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ።
ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”
ውሾች፣ አስማተኞች፣ ሴሰኞች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸትን የሚወድዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።