ልጅን ከመቅጣት ወደ ኋላ አትበል፤ በአርጩሜ ብትገርፈው አይሞትም።
በአርጩሜ ከመቅጣት የሚሳሳለት ልጁን ይጠላል፤ የሚወድደው ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል።
ገና ተስፋ ሳለ፣ ልጅህን ሥርዐት አስይዘው፤ ሲሞት ዝም ብለህ አትየው።
ቂልነት በሕፃን ልብ ታስሯል፤ የተግሣጽ በትር ግን ከርሱ ያርቅለታል።
ልብህን ለምክር፣ ጆሮህንም ለዕውቀት ቃል ስጥ።
የተግሣጽ በትር ጥበብን ታጐናጽፋለች፤ መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።
ልጅህን ቅጣው፤ ሰላም ይሰጥሃል፤ ነፍስህንም ደስ ያሰኛታል።
እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ ይዟችኋልና የተግሣጽን ምክር ታገሡ፤ ለመሆኑ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?