ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፤ የቍጣውም በትር ይጠፋል።
እኔ እንዳየሁ ክፋትን የሚያርሱ፣ መከራንም የሚዘሩ ያንኑ ያጭዳሉ።
ጻድቃን እጃቸውን ለክፋት እንዳያነሡ፣ የክፉዎች በትረ መንግሥት፣ ለጻድቃን በተመደበች ምድር ላይ አያርፍም።
የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፤ የዕቅዳቸውንም ውጤት ይጠግባሉ።
የቂል ሰው ንግግር ለጀርባው በትር ታስከትልበታለች፤ የጥበበኛ ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።
በአንተ ላይ ያመጣሁትን ቅጣት በጥቂት ጊዜ ውስጥ አቆማለሁ፤ በእነርሱም ላይ መቅሠፍቴን አመጣለሁ።”
“የቍጣዬ በትር ለሆነ፣ የመቅሠፍቴም ዱላ በእጁ ላለው ለአሦራዊው ወዮለት!
እናንተ ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ የመታችሁ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁ ደስ አይበላችሁ፤ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፤ ፍሬውም ተወርዋሪ መርዘኛ እባብ ይሆናል።
የእግዚአብሔር ድምፅ አሦርን ያስደነግጣል፤ በትሩም ይመታቸዋል።
ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፣ የከበዳቸውን ቀንበር፣ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።
እናንተ ግን ክፋትን ዘራችሁ፤ ኀጢአትንም ዐጨዳችሁ፤ የሐሰትንም ፍሬ በላችሁ። በራሳችሁ ጕልበት፣ በተዋጊዎቻችሁም ብዛት ታምናችኋልና፣
“ነፋስን ይዘራሉ፤ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤ አገዳው ዛላ የለውም፤ ዱቄትም አይገኝበትም፤ እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ ባዕዳን ይበሉታል።