የቀድሞ አባቶችህ ያስቀመጡትን፣ የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ።
ሰዎች ድንበር ይገፋሉ፤ የሰረቁትን መንጋ ያሰማራሉ።
የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ፤ አባት የሌላቸውንም ልጆች መሬት አትግፋ፤
በጻድቅ ሰው ቤት ላይ እንደ ወንበዴ አታድፍጥ፤ መኖሪያውንም በድንገት አታጥቃ፤
አምላክህ እግዚአብሔር እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ለአንተ በሚተላለፍልህ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አታንሣ።
“የባልንጀራውን የድንበር ድንጋይ ከቦታው የሚያንቀሳቅስ የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።