የምክርና የዕውቀት ቃል የሆኑ፣ መልካም ሠላሳ ትምህርቶችን አልጻፍሁልህምን?
የእግዚአብሔር ቃል የጠራ ቃል ነው፤ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ፣ በምድር ላይ በከውር እንደ ተፈተነ ብር ነው።
የምናገረው ጠቃሚ ነገር ስላለኝ አድምጡኝ፤ ቀና ነገር ለመናገር ከንፈሮቼን እከፍታለሁ።
ሰባኪው ትክክለኛውን ቃል ለማግኘት ተመራመረ፤ የጻፈውም ቅንና እውነት ነበረ።
በሕጌ ውስጥ ያለውን ብዙውን ነገር ጻፍሁላቸው፤ እነርሱ ግን እንደ እንግዳ ነገር ቈጠሩት።