የልብ ንጽሕናን ለሚወድድና ንግግሩም ሞገስ ላለው ሰው፣ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።
የናታን ልጅ ዓዛርያስ፣ የአውራጃ ገዦች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ዛቡድ፣ ካህንና የንጉሡ የቅርብ አማካሪ፤
አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕርግ ከንጉሡ ከጠረክሲስ ቀጥሎ ሁለተኛ፣ ከአይሁድ መካከልም ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ሰው ነበር፤ ለወገኖቹ መልካም በማድረጉና ለአይሁድም ሁሉ ደኅንነት የቆመ በመሆኑ፣ በብዙዎቹ አይሁድ ወገኖቹ ዘንድ እጅግ የተከበረ ነበር።
ከእኔ ጋራ ይኖሩ ዘንድ፣ ዐይኖቼ በምድሪቱ ታማኞች ላይ ናቸው፤ በፍጹም መንገድ የሚሄድ፣ እርሱ ያገለግለኛል።
ንጹሕ እጅና ቅን ልብ ያለው፤ ነፍሱን ለሐሰት ነገር የማያስገዛ፤ በውሸት የማይምል።
አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ፤ ከንፈሮችህም የጸጋ ቃል ያፈልቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባርኮሃል።
ጠቢብ አገልጋይ ንጉሥን ደስ ያሰኛል፤ አሳፋሪ አገልጋይ ግን ቍጣውን በራሱ ላይ ያመጣል።
ነገሥታት በታማኝ ከንፈሮች ደስ ይላቸዋል፤ ጽድቅ የሚናገረውን ሰው ይወድዱታል።
የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ የማይታመኑትን ሰዎች ቃል ግን እርሱ ከንቱ ያደርጋል።
ከጠቢብ አፍ የሚወጣ ቃል ባለሞገስ ነው፤ ሞኝ ግን በገዛ ከንፈሩ ይጠፋል፤
ከዚያም ንጉሡ ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን በባቢሎን አውራጃ ላይ ሾማቸው።
ልባቸው ንጹሕ የሆነ ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።
ሁሉም ስለ እርሱ በበጎ ይናገሩ ነበር፤ ደግሞም ከአንደበቱ በሚወጣ የጸጋ ቃል እየተገረሙ፣ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።