ክፉ ሰው ቀኑን ሙሉ ይመኛል፤ ጻድቅ ግን አንዳች ሳያስቀር ይሰጣል።
ማር፣ ርጎ፣ በጎችና የላም አይብ እንዲበሉ ለዳዊትና ለሕዝቡ አመጡላቸው፤ ይህን ያደረጉትም፣ “ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቧል፤ ደክሟል፤ ተጠምቷል” በማለት ነው።
ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣ ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል።
በልግስና ለድኾች ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል፤ ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
ሁልጊዜ ቸር ነው፤ ያበድራልም፤ ልጆቹም የተባረኩ ይሆናሉ።
ለሚለምንህ ስጥ፤ ከአንተም ሊበደር የሚሻውን ፊት አትንሣው።
ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ለተቸገሩት የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በገዛ እጆቹ በጎ የሆነውን እየሠራ ለማግኘት ይድከም።