በጠቢብ ቤት ምርጥ ምግብና ዘይት ተከማችቶ ይገኛል፤ ሞኝ ሰው ግን ያለ የሌለውን ያሟጥጣል።
የዋጠውን ሀብት ይተፋል፤ እግዚአብሔርም መልሶ ከሆዱ ያወጣዋል።
የለፋበትን ሳይበላው ይመልሳል፤ ከንግዱም ባገኘው ትርፍ አይደሰትም፤
ሀብትና ብልጽግና በቤቱ ይሞላል፤ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።
ጠላቶቼ እያዩ፣ በፊቴ ማእድ አዘጋጀህልኝ፤ ራሴን በዘይት ቀባህ፤ ጽዋዬም ሞልቶ ይፈስሳል።
የእግዚአብሔር በረከት ብልጽግናን ታመጣለች፤ መከራንም አያክልባትም።
ጠቢባን ብልጽግና ዘውዳቸው ነው፤ የሞኞች ቂልነት ግን ፍሬው ከንቱነት ነው።
የጻድቃን ቤት በብዙ ሀብት የተሞላ ነው፤ የክፉዎች ገቢ ግን መከራን ታመጣባቸዋለች።
ትሕትናና እግዚአብሔርን መፍራት፣ ሀብትን፣ ክብርንና ሕይወትን ያስገኛል።
ለሚወድዱኝ ብልጽግና እሰጣለሁ፤ ግምጃ ቤታቸውንም እሞላለሁ።
ግብዣ ለሣቅ ያዘጋጃል፤ ወይንም ሕይወትን ያስደስታል፤ ገንዘብም ካለ ሁሉ ነገር አለ።
አምላክ ለሰው ባለጠግነትና ሀብት መስጠቱ፣ እንዲደሰትበትም ማስቻሉ፣ ዕጣውን እንዲቀበልና በሥራውም እንዲደሰት ማድረጉ፣ ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።
ጥበብ እንደ ርስት መልካም ነገር ነው፤ ጠቃሚነቱም ፀሓይን ለሚያዩ ሰዎች ነው።
ከተገደሉት ጋራ የነበሩ ዐሥር ሰዎች ግን እስማኤልን፣ “እባክህ አትግደለን! በዕርሻችን ውስጥ የሸሸግነው ስንዴና ገብስ፣ የወይራ ዘይትና ማር ስላለን እባክህን አትግደለን” አሉት። እርሱም ተዋቸው፤ ከሌሎቹም ጋራ አልገደላቸውም።
ዝንጉዎቹ አስተዋዮቹን፣ ‘መብራታችን ሊጠፋብን ስለ ሆነ፣ ከዘይታችሁ ስጡን’ አሏቸው።
እርሱም ያለውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ፣ በዚያ አገር ሁሉ ጽኑ ራብ ሆነ፤ ይቸገርም ጀመር።
ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “አንድ ሀብታም ሰው አንድ መጋቢ ነበረው፤ ይኸው መጋቢ የሀብታሙን ሰው ንብረት እንደሚያባክን ለዚሁ ሰው ወሬ ደረሰው።
መልካም ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ነገር መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ካከማቸው ክፉ ነገር ክፉውን ያወጣል፤ ሰው በልቡ ሞልቶ የተረፈውን በአፉ ይናገራልና።