ምክር ጠይቀህ ዕቅድ አውጣ፤ ጦርነት የምትገጥም ከሆነ መመሪያ ተቀበል።
አሁንም የራስሽንና የልጅሽን የሰሎሞንን ሕይወት እንዴት ማዳን እንደምትችዪ ልምከርሽ፤
የጦር ስልትና ኀይል አለኝ ትላለህ፤ ነገር ግን ባዶ ቃል ብቻ ትናገራለህ። በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተደግፈህ ነው?
በአመራር ጕድለት መንግሥት ይወድቃል፤ የመካሮች ብዛት ግን ድልን ርግጠኛ ያደርጋል።
ምክር ሲጓደል ዕቅድ ይፋለሳል፤ በብዙ አማካሪዎች ግን ይሳካል።
ጦርነት ለመግጠም መልካም ምክር፣ ድል ለማድረግም ብዙ አማካሪዎች ያስፈልጋሉ።
ወደ ፍርድ አደባባይ በችኰላ አታውጣው፤ ባልንጀራህ ካሳፈረህ፣ ኋላ ምን ይውጥሃል?
“ወይም አንድ ንጉሥ ከሌላው ንጉሥ ጋራ ጦርነት ሊገጥም በሚነሣበት ጊዜ፣ ሃያ ሺሕ ሰራዊት አስከትቶ የሚመጣበትን ንጉሥ፣ በዐሥር ሺሕ ሰራዊት መመከት እንደሚችል ተቀምጦ የማይመክር ማን ነው?
ያየም ሁሉ፣ “እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ ጀምሮ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልታየም፤ አልተደረገም፤ ምን ማድረግ እንዳለብንም በነገሩ አስቡበት፤ ተመካከሩበት” ተባባሉ።
እስራኤላውያን ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርም፣ “ብንያማውያንን ለመውጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” ሲሉ ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ” ብሎ መለሰ።
እስራኤላውያን ወጥተው እስኪመሽ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት አለቀሱ፤ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመግጠም እንደ ገና እንውጣን?” ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን፤ ውጡና ግጠሟቸው” ብሎ መለሰላቸው።
አሁንም እናንተ እስራኤላውያን ሁሉ በጕዳዩ ላይ ተወያዩበት፤ ፍርዳችሁንም ስጡ።”
ምነው ይህን ሕዝብ የማዝዘው እኔ በሆንሁ ኖሮ! አቢሜሌክን አስወግደው ነበር፤ ‘ሰራዊትህን አብዝተህ ውጣ!’ እለው ነበር።”