ድኻ በሥጋ ዘመዶቹ ሁሉ የተጠላ ነው፤ ታዲያ ወዳጆቹማ የቱን ያህል ይሸሹት! እየተከታተለ ቢለማመጣቸውም፣ ከቶ አያገኛቸውም።
ከቍስሌ የተነሣ ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ሸሹኝ፤ ጎረቤቶቼም ርቀው ቆሙ።
ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ሊያጠፉኝ ዛቱ፤ ቀኑንም ሙሉ ተንኰል ይሸርባሉ።
ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤ ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።
የሚቀርቡኝ ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅህ፤ እንዲጸየፉኝም አደረግህ፤ ተከብቤአለሁ፤ ማምለጥም አልችልም፤
የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ ድኽነት ግን የድኾች መጥፊያ ናት።
ድኾችን ወዳጆቻቸው እንኳ ይጠሏቸዋል፤ ባለጠጎች ግን ብዙ ወዳጆች አሏቸው።
ድኻ በመለማመጥ ምሕረት ይለምናል፤ ሀብታም ግን በማናለብኝነት ይመልሳል።
ሀብት ብዙ ወዳጅ ታፈራለች፤ ድኻን ግን ወዳጁ ገሸሽ ያደርገዋል።
ሰው የድኾችን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን ቢዘጋ፣ እርሱም ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።
የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤ መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።
እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ፤ እናንተን የሚያስጨንቋችሁ ሀብታሞች አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤት የሚጐትቷችሁስ እነርሱ አይደሉምን?