ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ ውሸት የሚነዛም ሳይቀጣ አይቀርም።
ሽማግሌው ነቢይ ግን፣ “እኔም እኮ እንደ አንተው ነቢይ ነኝ፤ መልአክ በእግዚአብሔር ቃል፣ ‘እንጀራ እንዲበላና ውሃ እንዲጠጣ መልሰህ ወደ ቤትህ አምጣው’ ብሎኝ ነው” አለው፤ ነገር ግን ውሸቱን ነበር።
አሁን ግን በደል እንደሌለበት ሰው አትተወው፤ ጥበበኛ ነህና መደረግ ያለበትን ታውቃለህ፤ ሽበቱን በደም ወደ መቃብር አውርድ።”
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፋታቸው የተነሣ እንዳያመልጡ፣ ሕዝቦቹን በቍጣህ ጣላቸው።
በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
“የሐሰት ወሬ አትንዛ፤ ተንኰል ያለበትን ምስክርነት በመስጠት ክፉውን ሰው አታግዝ።
እውነተኛ ምስክር ሕይወት ያድናል፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን አባይ ነው።
ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይዘከዝካል።
ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ ውሸት የሚነዛም ይጠፋል።
ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤ እውነቱን የሚናገር ግን ጸንቶ ይኖራል።
በውሸት ላይ ውሸት የሚጨምር ሐሰተኛ ምስክር፣ በወንድማማቾች መካከል ጠብን የሚጭር ሰው።
በንጉሡ ትእዛዝ፣ ዳንኤልን በሐሰት የከሰሱትን ሰዎች፣ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋራ አምጥተው፣ በአንበሶቹ ጕድጓድ ውስጥ ጣሏቸው፤ ገና ወደ ጕድጓዱ መጨረሻ ሳይደርሱም፣ አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ ዐጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።
የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አታንሣ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን በደል አልባ አያደርገውምና።