ለፌዘኞች ቅጣት፣ ለሞኞችም ጀርባ ጅራፍ ተዘጋጅቷል።
ኤልሳዕም ዘወር ብሎ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ ከዚያም ሁለት እንስት ድቦች ከዱር ወጥተው ከልጆቹ አርባ ሁለቱን ሰባበሯቸው።
ብፁዕ ነው፣ በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣ በኀጢአተኞች መንገድ የማይቆም፣ በፌዘኞችም ወንበር የማይቀመጥ፤
“እናንተ አላዋቂዎች፤ ማስተዋል የሌለበት መንገዳችሁን እስከ መቼ ትወድዱታላችሁ? ፌዘኞች በፌዝ ደስ የሚሰኙት፣ ሞኞችስ ዕውቀትን የሚጠሉት እስከ መቼ ነው?
እኔ ደግሞ በመከራችሁ እሥቅባችኋለሁ፤ መዓት በሚወርድባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ፤
ጥበብ በአስተዋይ ሰው ከንፈር ትገኛለች፤ በትር ግን ለልበ ቢስ ሰው ጀርባ ነው።
መቶ ግርፋት ሞኝን ከሚሰማው ይልቅ፣ ተግሣጽ ለአስተዋይ ጠልቆ ይሰማል።
የሞኝ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤ አፉም በትር ይጋብዛል።
ለፈረስ ዐለንጋ፣ ለአህያ መሸበቢያ፣ ለሞኝ ጀርባም በትር ይገባዋል።
እርሱ በዕቡያን ፌዘኞች ላይ ያፌዛል፤ ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል።
ለዕርድ እንደሚነዳ በሬ፣ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ አጋዘን፣ ሳያንገራግር ተከተላት፤
ጠቢብ ብትሆን ጥበበኛነትህ ለራስህ ነው፤ ፌዘኛ ብትሆን የምትጐዳው ያው አንተው ነህ።”
እንግዲህ ፌዛችሁን አቁሙ፤ አለዚያ እስራታችሁ ይጸናባችኋል፤ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ መላውን ምድር ለማጥፋት ያወጀውን ዐዋጅ ሰምቻለሁ።
ጨካኞች እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ፌዘኞችም በንነው ይጠፋሉ፤ ለክፋት ያደፈጡ ሁሉ ይወገዳሉ።
በደለኛው ሰው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ፣ ዳኛው መሬት ላይ ያጋድመው፤ ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ግርፋት እርሱ ባለበት ይገረፍ።
ምክንያቱም ጌታ የሚወድደውን ይገሥጻል፤ እንደ ልጅ የሚቀበለውንም ይቀጣል።”