ግልፍተኛ ሰው ቅጣትን መቀበል ይገባዋል፤ በምሕረት ካለፍኸው ሌላም ጊዜ አይቀርልህም።
ቂሉን ሰው ብስጭት ይገድለዋል፤ ቂሉንም ቅናት ያጠፋዋል።
ገና ተስፋ ሳለ፣ ልጅህን ሥርዐት አስይዘው፤ ሲሞት ዝም ብለህ አትየው።
ምክርን ስማ፤ ተግሣጽን ተቀበል፤ በመጨረሻም ጠቢብ ትሆናለህ።
ራሱን የማይቈጣጠር ሰው፣ ቅጥሯ እንደ ፈረሰ ከተማ ነው።
ቍጡ ሰው ጠብን ይጭራል፤ ግልፍተኛም ብዙ ኀጢአት ይሠራል።