ጥበብ ሰውን ታጋሽ ታደርገዋለች፤ በደልን ንቆ መተውም መከበሪያው ነው።
ለዚህ ለዚህ የደማስቆ ወንዞች አባናና ፋርፋር ከየትኞቹም የእስራኤል ውሆች አይሻሉምን? ለመታጠብ ለመታጠብማ በእነርሱ ታጥቤ መንጻት አልችልምን?” ስለዚህ በቍጣ ተመለሰ።
ሐሜተኛ ምስጢር አይጠብቅም፤ ታማኝ ሰው ግን ምስጢር ይጠብቃል።
ቂል ሰው ቍጣው ወዲያውኑ ይታወቅበታል፤ አስተዋይ ሰው ግን ስድብን ንቆ ይተዋል።
ታጋሽ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ ግልፍተኛ ሰው ግን ቂልነትን ያሳያል።
ግልፍተኛ ሰው ጠብ ያነሣሣል፤ ታጋሽ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል።
ታጋሽ ሰው ከጦረኛ፣ ስሜቱን የሚገዛም ከተማን በጕልበቱ ከሚይዝ ይበልጣል።
ጠብ መጫር ግድብን እንደ መሸንቈር ነው፤ ስለዚህ ጠብ ከመጫሩ በፊት ከነገር ራቅ።
“ለደረሰብኝ በደል ብድሬን ባልመልስ!” አትበል፤ እግዚአብሔርን ጠብቅ፤ እርሱ ይታደግሃል።
ከጠብ መራቅ ለሰው ክብሩ ነው፤ ቂል ሁሉ ግን ለጥል ይቸኵላል።
ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማም ውሃ አጠጣው።
ሞኝ ሰው ቍጣውን ያለ ገደብ ይለቅቀዋል፤ ጠቢብ ሰው ግን ራሱን ይቈጣጠራል።
እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ፣ እናንተም ይቅር ተባባሉ፤ እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ይህን አስተውሉ፤ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየ፣ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤