Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ምሳሌ 17:3

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ብር በማቅለጫ፣ ወርቅም በከውር፤ እግዚአብሔርም ልብን ይፈትናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አምላኬ ሆይ፤ ልብን እንደምትመረምርና ቅንነትን እንደምትወድድ ዐውቃለሁ፤ እኔም ይህን ሁሉ የሰጠሁት በበጎ ፈቃድና በቀና መንፈስ ነው። አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በበጎ ፈቃዱ እንዴት እንደ ሰጠ አይቻለሁ።

ግን እኔ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።

“የብር ማዕድን የሚወጣበት፣ ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ።

እግዚአብሔር ሆይ፤ መርምረኝ፤ ልቤንም ዕወቅ፤ ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈትነኝ፤ መርምረኝም፤ ልቤንና ውስጤን መርምር፤

አምላክ ሆይ፤ አንተ ፈተንኸን፤ እንደ ብርም አነጠርኸን።

ሲኦልና የሙታን ዓለም በእግዚአብሔር ፊት የተገለጡ ናቸው፤ የሰዎች ልብማ የቱን ያህል የታወቀ ነው!

ለሰው መንገዱ ሁሉ ንጹሕ መስሎ ይታየዋል፤ መነሻ ሐሳቡ ግን በእግዚአብሔር ይመዘናል።

ጠቢብ አገልጋይ በወራዳ ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤ ከወንድማማቾቹም እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል።

ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል።

ብር በማቅለጫ፣ ወርቅም በከውር እንደሚፈተን፤ ሰውም በአንደበት ምስጋና ይፈተናል።

እነሆ፤ እንደ ብር ባይሆንም አንጥሬሃለሁ፤ በመከራ እቶን ፈትኜሃለሁ።

“እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፣ እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት፣ ልብን እመረምራለሁ፤ የአእምሮንም ሐሳብ እፈትናለሁ።”

“የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ቤት የብረት ዝቃጭ ሆነብኝ፤ ሁሉም በከውር ውስጥ ቀልጦ እንደሚቀር መዳብ፣ ቈርቈሮ፣ ብረትና እርሳስ ናቸው፤ እነዚህ ከብር የሚወጡ ዝቃጭ ናቸው።

ጥበበኛ ከሆኑ ሰዎች አንዳንዶቹ ይሰናከላሉ፤ ይህም እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የጠሩ፣ የነጠሩና እንከን የሌለባቸው ይሆኑ ዘንድ ነው፤ የተወሰነው ጊዜ ገና አልደረሰምና።

ይህን አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አመጣለሁ፤ እንደ ብር አነጥራቸዋለሁ፤ እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱ ስሜን ይጠራሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ፤ እኔም፣ ‘ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤ እነርሱም፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ነው’ ይላሉ።”

በመጨረሻ መልካም እንዲሆንልህ፣ አንተን ትሑት ለማድረግና ለመፈተን፣ አባቶችህ ፈጽሞ የማያውቁትን መና በምድረ በዳ መገበህ።

አምላክህ እግዚአብሔር ትእዛዞቹን መጠበቅህንና በልብህ ያለውን ለማወቅ፣ ትሑት ሊያደርግህና ሊፈትንህ በእነዚህ አርባ ዓመታት በዚህ ምድረ በዳ ጕዞህ ሁሉ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።

እነዚህ ነገሮች በእናንተ ላይ የደረሱት፣ በእሳት ተፈትኖ ቢጠራም፣ ጠፊ ከሆነው ወርቅ ይልቅ እጅግ የከበረው እምነታችሁ፣ እውነተኛ መሆኑ እንዲረጋገጥና ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፣ ክብርንና ውዳሴን እንዲያስገኝላችሁ ነው።

ልጆቿንም በሞት እቀጣቸዋለሁ። ከዚያም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እኔ ልብንና ሐሳብን የምመረምር መሆኔን ይረዳሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እከፍላችኋለሁ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች