ቂል እንኳ ዝም ቢል ጠቢብ፣ አንደበቱንም ቢገዛ አስተዋይ ይመስላል።
ምነው ዝም ብትሉ! ያ ከጥበብ ይቈጠርላችሁ ነበር።
እንግዲህ እነርሱ መልስ ስላጡ፣ ጸጥ ብለውም ስለ ቆሙ፣ በትዕግሥት ልጠብቅን?
የጠቢብ አንደበት ዕውቀትን ታወድሳለች፤ የሞኞች አንደበት ግን ቂልነትን ያፈልቃል።
ወዳጅነትን የማይፈልግ ሰው የራሱን ፍላጎት ብቻ ይከተላል፤ ቅን የሆነውንም ፍርድ ሁሉ ይቃወማል።
ሞኙም ቃልን ያበዛል። የሚመጣውን የሚያውቅ ሰው የለም፤ ከርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ማን ሊነግረው ይችላል?
ሞኝ በጐዳና ሲሄድ ልበ ቢስ ነው፤ ጅል መሆኑንም ለማንም ይገልጻል።
በሥራ ብዛት ሕልም እንደሚታይ፣ ብዙ ቃል ባለበትም የሞኝ ንግግር ይገለጣል።