ጠማማ ልብ ያለው ሰው አይሳካለትም፤ በአንደበቱ የሚቀላምድም መከራ ላይ ይወድቃል።
ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣ ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ።
በተንኰለኛ ዐይን የሚጠቅስ ሐዘን ያስከትላል፤ ለፍላፊ ቂልም ወደ ጥፋት ያመራል።
ጠቢባን ዕውቀት ያከማቻሉ፤ የቂል አንደበት ግን ጥፋትን ይጋብዛል።
የጻድቃን አንደበት ጥበብን ያፈልቃል፤ ጠማማ ምላስ ግን ትቈረጣለች።
ግፈኛ ተስፋ የለውምና፤ የክፉዎችም መብራት ድርግም ብላ ትጠፋለች።
እግዚአብሔር ጠማማን ሁሉ ይጸየፋልና፤ ለቅን ሰው ግን ምስጢሩን ይገልጥለታል።
እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፤ እኔም ትዕቢትንና እብሪትን፣ ክፉ ጠባይንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ።
ከጠቢብ አፍ የሚወጣ ቃል ባለሞገስ ነው፤ ሞኝ ግን በገዛ ከንፈሩ ይጠፋል፤