ልበ ቢስ ሰው ሰው ቃል በመግባት እጅ ይመታል፤ ለወዳጁም ዋስ ይሆናል።
ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሚሆን መከራ ያገኘዋል፤ ዋስትና ለመስጠት እጅ የማይመታ ግን ምንም አይደርስበትም።
ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሆነውን ልብሱን ግፈፈው፤ ለባዕድ ሴት የተዋሰውን በቃሉ ዐግተው።
ሀብቱን ለማካበት ድኻን የሚበድል፣ ለባለጠጋም ስጦታ የሚያቀርብ፣ ሁለቱም ይደኸያሉ።