ደስ የሚያሰኝ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ለነፍስ ጣፋጭ፣ ለዐጥንትም ፈውስ ነው።
ቃልህ ለምላሴ ምንኛ ጣፋጭ ነው! ለአፌም ከማር ወለላ ይልቅ ጣዕም አለው።
ከወርቅ ይልቅ የከበረ፣ እጅግ ከጠራ ወርቅም የተሻለ ነው፤ ከማር ይልቅ ይጣፍጣል፤ ከማር ወለላም ይበልጥ ይጥማል።
ግድ የለሽ ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል፤ የጠቢብ አንደበት ግን ፈውስን ያመጣል።
ሰው ተገቢ መልስ በመስጠት ደስታን ያገኛል፤ በወቅቱም የተሰጠ ቃል ምንኛ መልካም ነው!
እግዚአብሔር የክፉውን ሰው ሐሳብ ይጸየፋል፤ የንጹሓን ሐሳብ ግን ደስ ያሠኘዋል።
ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኀኒት ነው፤ የተሰበረ መንፈስ ግን ዐጥንትን ያደርቃል።
ከንፈሮችህ ትክክሉን ቢናገሩ፣ ውስጣዊ ሁለንተናዬ ሐሤት ያደርጋል።
ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤ የወዳጅ ማስደሰትም ከቅን ምክሩ ይመነጫል።
ይህም ለሰውነትህ ጤንነትን፣ ለዐጥንትህም ልምላሜን ያመጣልሃል።
ለሚያገኘው ሕይወት፤ ለመላው የሰው አካልም ጤንነት ነውና።
ሰባኪው ትክክለኛውን ቃል ለማግኘት ተመራመረ፤ የጻፈውም ቅንና እውነት ነበረ።
ሙሽራዬ ሆይ፤ ከንፈሮችሽ የማር ወለላ ያንጠባጥባሉ፤ ከአንደበትሽም ወተትና ማር ይፈልቃል፤ የልብስሽም መዐዛ እንደ ሊባኖስ ሽታ ነው።
ቃልህ በተገኘ ጊዜ በላሁት፤ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ ተጠርቻለሁና፣ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነልኝ።
ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትውረድ፤ ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በቡቃያ ሣር ላይ እንደ ካፊያ፣ ለጋ ተክልም ላይ እንደ ከባድ ዝናብ ይውረድ።
ትንሿንም መጽሐፍ ከመልአኩ እጅ ተቀብዬ በላኋት፤ በአፌ እንደ ማር ጣፈጠች፤ ከበላኋት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ፤