ሐሜተኛ ምስጢር አይጠብቅም፤ ታማኝ ሰው ግን ምስጢር ይጠብቃል።
ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤ አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው።
ልበ ቢስ ባልንጀራውን ያንኳስሳል፤ አስተዋይ ግን አንደበቱን ይገዛል።
አስተዋይ ሰው ዕውቀቱን ይሰውራል፤ የሞኞች ልብ ግን ቂልነትን ይነዛል።
ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይዘከዝካል።
ጥበብ ሰውን ታጋሽ ታደርገዋለች፤ በደልን ንቆ መተውም መከበሪያው ነው።
ሐሜተኛ ምስጢር ያባክናል፤ ስለዚህ ለፍላፊን ሰው አርቀው።
ስለ ራስህ ጕዳይ ከባልንጀራህ ጋራ በምትከራከርበት ጊዜ፣ የሌላውን ሰው ምስጢር አታውጣ፤
መኳንንቱ ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት፤ እርሱም ንጉሡ ያዘዘውን ቃል ሁሉ ነገራቸው፤ ከንጉሡ ጋራ የተነጋገሩትን ነገር የሰማ አንድም ሰው ስላልነበረ፣ ከዚህ በላይ አላነጋገሩትም።
“ ‘በሕዝብህ መካከል ሐሜት አትንዛ። “ ‘የባልንጀራህን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም ነገር አታድርግ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
በተጨማሪም ሥራ መፍታትንና ከቤት ቤት መዞርን ይለምዳሉ፤ ሥራ ፈት መሆን ብቻ ሳይሆን፣ የማይገባውን እየተናገሩ ሐሜተኞችና በሰው ጕዳይም ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።
ሰዎቹም፣ “የእናንተን ሞት ለእኛ ያድርገው! እኛ የምናደርገውን ሁሉ ካልተናገራችሁ፣ እግዚአብሔር ምድሪቱን በሚሰጠን ጊዜ፣ በጎነትና ታማኝነት እናሳይሻለን” አሏት።
እኛ የምናደርገውን ብትናገሪ ግን፣ ካስማልሽን መሐላ ነጻ እንሆናለን።”