ክፉ ሰው የፈራው ይደርስበታል፤ ጻድቅ የሚመኘው ይፈጸምለታል።
የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ላይ ይጮኻል፤ በሰላም ጊዜ ቀማኞች አደጋ ያደርሱበታል።
የፈራሁት ነገር መጥቶብኛል፤ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል።
ለሚፈሩት ፍላጎታቸውን ይፈጽማል፤ ጩኸታቸውን ይሰማል፤ ያድናቸዋልም።
የልቡን መሻት ሰጠኸው፤ የከንፈሮቹንም ልመና አልከለከልኸውም። ሴላ
በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።
እኔ ደግሞ በመከራችሁ እሥቅባችኋለሁ፤ መዓት በሚወርድባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ፤
መዓት እንደ ማዕበል ሲያናውጣችሁ፣ መከራም እንደ ዐውሎ ነፋስ ሲጠራርጋችሁ፣ ሥቃይና ችግር ሲያጥለቀልቃችሁ አፌዝባችኋለሁ።
እግዚአብሔር የክፉዎችን መሥዋዕት ይጸየፋል፤ የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሠኘዋል።
ስለዚህ ችግር እንዲደርስባቸው አደርጋለሁ፤ የፈሩትንም አመጣባቸዋለሁ፤ በተጣራሁ ጊዜ የመለሰ፣ በተናገርሁ ጊዜ ያደመጠ ሰው የለምና። በፊቴ ክፉ ነገር አደረጉ፤ የሚያስከፋኝንም መረጡ።”
ሰይፍን ፈርታችኋል፤ እኔም ሰይፍ እልክባችኋለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ይህ ሁሉ በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ ደረሰ፤
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ ይጠግባሉና።
ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።
እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ለምኑ ትቀበላላችሁ፤ ደስታችሁም ሙሉ ይሆናል።
የሚቀረው ግን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚበላ ብርቱ እሳት መጠበቅ ብቻ ነው።