ውድ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በየዐይነቱ እናገኛለን፤ ቤቶቻችንንም በዝርፊያ እንሞላለን፤
እንደ መቃብር፣ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ፣ ከነሕይወታቸው በሙሉ እንዋጣቸው፤
ከእኛ ጋራ ዕጣህን ጣል፤ የጋራ ቦርሳ ይኖረናል” ቢሉህ፣
ያላግባብ ለጥቅም የሚሯሯጡ ሁሉ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤ የሕይወታቸው መጥፊያም ይኸው ነው።
በተዋረደ መንፈስ ከተጨቈኑት ጋራ መሆን፣ ከትዕቢተኞች ጋራ ብዝበዛን ከመካፈል ይሻላል።
“ቅሚያንና ዝርፊያን በምሽጋቸው ውስጥ የሚያከማቹ፣ በጎ ነገር ማድረግን አያውቁም፤” ይላል እግዚአብሔር።
ለአዛጦን ምሽግ፣ ለግብጽም ምሽግ እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤ በውስጧ ያለውን ታላቅ ሁከት፣ በሕዝቧም መካከል ያለውን ግፍ እዩ።”
አንበሳው ለግልገሎቹ የሚበቃውን ያህል ገደለ፤ ለእንስቶቹም ዐንቆ ገደለላቸው፤ የገደለውን በማረፊያ ቦታው፣ የነጠቀውንም በዋሻው ሞልቶታል።
‘የዚህ የአሁኑ ቤት ክብር ከቀድሞው ቤት ክብር ይበልጣል’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ‘በዚህም ቦታ ሰላምን እሰጣለሁ’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”
ደግሞም፣ “የሰው ሕይወቱ በሀብቱ ብዛት የተመሠረተ ስላልሆነ ተጠንቀቁ፤ ከስግብግብነትም ሁሉ ራሳችሁንም ጠብቁ” አላቸው።