“ሌቦች ወደ አንተ ቢመጡ፣ ዘራፊዎችም በሌሊት ቢገቡ፣ የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ አይደለምን? ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ፣ ጥቂት ቃርሚያ አይተዉምን? አንተ ግን ምንኛ ጥፋት ይጠብቅሃል!
“እስራኤል ሆይ፤ ክብርህ በኰረብቶችህ ላይ ተወግቶ ሞቷል፤ ኀያላኑ እንዴት እንደዚህ ይውደቁ!
አንተ የንጋት ልጅ፣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፤ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አንተ ቀድሞ መንግሥታትን ያዋረድህ፣ እንዴት ወደ ምድር ተጣልህ!
ሆኖም የወይራ ዛፍ ሲመታ፣ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በቅርንጫፍ ራስ ላይ እንደሚቀር፣ አራት ወይም ዐምስት ፍሬ ችፍግ ባለው ቅርንጫፍ ላይ እንደሚቀር፣ እንዲሁ ጥቂት ቃርሚያ ይተርፋል” ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።
የወይራ ዛፍ ሲመታ፣ የወይንም ዘለላ ሲቈረጥ ቃርሚያ እንደሚቀር ሁሉ፣ በምድሪቱ ላይ፣ በሕዝቦችም ላይ እንዲሁ ይሆናል።
ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ፣ ጥቂት ወይን አያስቀሩምን? ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፣ የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ብቻ አይደለምን?
የምድር ሁሉ መዶሻ፣ እንዴት ተሰበረ! እንዴትስ ደቀቀ! በሕዝቦች መካከል፣ ባቢሎን እንዴት ባድማ ሆነች!
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የወይን ፍሬ ተሟጦ እንደሚቃረም፣ ከእስራኤል የተረፉትን እንዲሁ ይቃርሟቸው። ወይን ለቃሚ እንደሚለቅም፣ እጅህን ወደ ቅርንጫፎቹ ደጋግመህ ዘርጋ።”
በሕዝብ ተሞልታ የነበረችው ከተማ፣ እንዴት የተተወች ሆና ቀረች! በሕዝቦች መካከል ታላቅ የነበረችው፣ እርሷ እንዴት እንደ መበለት ሆነች! በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው፣ አሁን ባሪያ ሆናለች።
“ቴማን ሆይ፤ ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ፤ በዔሳውም ተራሮች ያለ ሁሉ፣ ተገድሎ ይጠፋል።
ለእኔ ወዮልኝ! የወይን ዕርሻ በሚቃረምበት ጊዜ፣ የበጋ ፍራፍሬ እንደሚለቅም ሰው ሆኛለሁ፤ የሚበላ የወይን ዘለላ የለም፤ የምንጓጓለት፣ ቶሎ የሚደርሰው በለስም አልተገኘም።
ያለ ሥጋት የኖረች፣ ደስተኛዪቱ ከተማ ይህች ናት፤ እርሷም በልቧ፣ “እኔ ብቻ ነኝ! ከእኔ በቀር ማንም የለም” ያለች፣ ታዲያ እንዴት የዱር አራዊት የሚመሰጉባት፣ ባድማ ሆና ቀረች? በአጠገቧ የሚያልፉ ሁሉ፣ ያፌዙባታል፤ እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል።
የወይን ተክልህን ፍሬ ስትሰበስብ ቃርሚያውን ለመሰብሰብ አትመለስበት፤ የቀረውን ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።
ሥቃይዋንም በመፍራት በሩቅ ቆመው እንዲህ ይላሉ፤ “ ‘አንቺ ታላቂቱ ከተማ ወዮልሽ! ወዮልሽ! አንቺ ባቢሎን ብርቱዪቱ ከተማ፣ ፍርድሽ በአንድ ሰዓት ውስጥ መጥቷል።’