አንዳንድ ጊዜ ደመናው በድንኳኑ ላይ የሚቈየው ለጥቂት ቀን ብቻ ነበር፤ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍራሉ፤ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ጕዞ ይጀምራሉ፤
ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነውና፤ እስከ መጨረሻው የሚመራንም እርሱ ነው።
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤
በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል።
እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረትም ለመጀመሪያ ጊዜ ተጓዙ።
እስራኤላውያን ጕዞ የሚጀምሩትም ሆነ የሚሰፍሩት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ነበር። ደመናው በድንኳኑ ላይ በሚቈይበት ጊዜ ሁሉ ከሰፈር አይንቀሳቀሱም ነበር።
ደመናው በድንኳኑ ላይ ብዙ ቀን ቢቈይም እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቃሉ እንጂ ተነሥተው አይጓዙም።
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ደመናው ከምሽት እስከ ንጋት ብቻ ይቈያል፤ ደመናው ንጋት ላይ ሲነሣም ጕዟቸውን ይጀምራሉ፤ ቀንም ይሁን ሌሊት ደመናው ከተነሣ ጕዞ ይጀምራሉ።
በመካከልህ ያለው አምላክህ እግዚአብሔር ታላቅና የሚያስፈራ አምላክ ስለ ሆነ አያስደንግጡህ።